Timran

ሁለንተናዊ ወቅታዊ የሰብአዊ መብቶች ግምገማ

ሁለንተናዊ ወቅታዊ ግምገማ የ193ቱን የተባበሩት መንግሥታት አባል ሀገራት የሰብአዊ መብት መዛግብትን የሚገመግም ሂደት ነው። 3ኛው ሁለንተናዊ ወቅታዊ የሰብአዊ መብቶች ግምገማ ዑደት በኢትዮጵያ ሴቶች የፖለቲካ ተሳትፎ ላይ ያተኮረ ነበር። ግምገማዎቹ በሕግ ማእቀፍ፣ በፖለቲካ ተሳትፎ እና በአቅም ግንባታ ተብለው ሊከፋፈሉ ይችላሉ። ሁሉን አቀፍ የሥርዓተ ጾታ እኩልነት ሕግ በማውጣት እና ሕገ መንግሥቱን በማሻሻል የሴቶችን የፖለቲካ ተሳትፎ የሕግ ማእቀፉን ለማጠናከር ምክረ ሐሳቦች ተሰጥተዋል። ኢትዮጵያ በፖለቲካ ተቋማት ውስጥ የሴቶችን ውክልና ለማሳደግ የሴቶች ብሔራዊ ፖሊሲ እና የምርጫ ሕግ ያሉ አዎንታዊ ሕጎችን አውጥታለች። የኢትዮጵያ መንግሥት የጾታ እኩልነትንና የሴቶችን ተጠቃሚነት ለማሳደግ ከፍተኛ ጥረት ቢያደርግም የኢትዮጵያ ሴቶች አሁንም በፖለቲካዊ ሂደቶች ውስጥ ለመግባት እና ለመሳተፍ ፈተናዎች ይገጥሟቸዋል። የሁለተናዊ ወቅታዊ የሰብአዊ መብቶች ግምገማ ሂደት እነዚህን ተግዳሮቶች ለመቅረፍ እና የሴቶችን የፖለቲካ ተሳትፎ ለማሻሻል የሚያስችሉ መንገዶችን ያሳያል።

በኢትዮጵያ የሕግ ማእቀፍ ውስጥ የሴቶችን መብት በፖለቲካ ሂደት ለማስተዋወቅ እና ለማስጠበቅ ከፍተኛ ለውጦች ተደርገዋል። የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት የሴቶችን የውሳኔ ሰጪ አካላት እኩል ተሳትፎ ለማረጋገጥ አዎንታዊ እርምጃዎችን ያዝዛል። የምርጫ አዋጁ የፖለቲካ ፓርቲዎች ቢያንስ 30 በመቶ የሚሆኑት እጩዎቻቸው ሴቶች መሆናቸውን እንዲያረጋግጡ ያስገድዳል። ኢትዮጵያ በፖለቲካ ተቋማት ውስጥ የሴቶችን ውክልና ለማሳደግ አዎንታዊ እርምጃ የሆኑ ሕጎችን አውጥታለች። የሀገሪቱ የሴቶች ብሔራዊ ፖሊሲ የሴቶችን ተሳትፎ በአመራር እና በውሳኔ ሰጪነት ለማሳደግ ያለመ ነው። እነዚህ ጥረቶች ቢኖሩም በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ሴቶች 30 በመቶውን የፓርላማ መቀመጫ ብቻ በመያዝ በቂ ውክልና የላቸውም። በፖለቲካዊ መዋቅሮች እና እንቅስቃሴዎች ውስጥ እኩል ውክልና ለማረጋገጥ እና የሥርዓተ-ጾታ እኩልነትን ለማጎልበት የበለጠ መሠራት አለበት።

የሴቶችን የፖለቲካ ተሳትፎ ለማሳደግ እና ድምፃቸው እንዲሰማ ለማድረግ በፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ፓርላማዎች እና የአካባቢ የመንግሥት አካላት የሴቶችን ውክልና የኮታ ሥርዓት በመዘርጋት ምክረ ሐሳቦች ተሰጥተዋል። ለሴቶች እጩ ተወዳዳሪዎች እና ተወካዮች ሥልጠና እና ድጋፍ መስጠት እና የፖለቲካ ፓርቲዎች የጾታ እኩልነትን በንቃት እንዲያሳድጉ ማበረታታት እና የሴቶችን መዋቅር እና እንቅስቃሴ ውስጥ ተሳትፎ ማድረግም እንዳለባቸው ተጠቁሟል። የሴቶችን በፖለቲካዊ ሂደቶች የመሳተፍ አቅምን ለማሻሻል በትምህርት፣ በግንዛቤ ማስጨበጫ እና በአመራር ልማት ዙሪያ ምክረ ሐሳቦች ተሰጥተዋል። እርምጃዎች የሴቶችን እኩል የትምህርት ተደራሽነት ማረጋገጥ፣ሥርዓተ ጾታ ተኮር ሥርዓተ ትምህርትን በትምህርት ቤቶች ማስተዋወቅ እና በሥርዓተ ጾታ ላይ የሚታዩ የተዛቡ አመለካከቶችን ለመቃወም የግንዛቤ ማስጨበጫ ዘመቻዎችን ማድረግን ያጠቃልላል። ለሴቶች መሪዎች ችሎታቸውንና በራስ መተማመንን ለማሳደግ የሥልጠና እና የማማከር መርሐ ግብሮችም ማከተት ያስፈልጋል። በተጨማሪም የበጎ አድራጎት ድርጅቶች እና ማኅበራት አዋጅ ቁጥር 1113/2011 የበጎ አድራጎት ድርጅቶች እና መያዶች የቦርድ አባላት 30 በመቶው ሴቶች እንዲሆኑ ይደነግጋል። በኢትዮጵያ የሴቶች የፖለቲካ ተሳትፎ የሀገሪቱ የዴሞክራሲ እድገት ወሳኝ ገጽታ ነው።

በ3ኛው ሁለንተናዊ ወቅታዊ የሰብአዊ መብቶች ግምገማ ዑደት ወቅት የኢትዮጵያ ሴቶችን የፖለቲካ ተሳትፎ ለማሻሻል በርካታ ምክረ ሐሳብ ተሰጥተዋል። ከእነዚህ መካከል:-
• ሴቶች በፖለቲካዊ ሕይወታቸው ውስጥ ያላቸውን አቅም ማጎልበት እና ተሳትፎአቸው አስፈላጊ በመሆኑ እኩል የትምህርት እና የጤና አገልግሎት ተጠቃሚ መሆናቸውን ማረጋገጥ፣
• የጾታ እኩልነትንና የሴቶችን መብት የሚያበረታቱ እንደ የኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት የሴቶች እና የወንዶች እኩልነት መብትን የሚያረጋግጡ ሕጎችንና ፖሊሲዎችን ማጽደቅ እና መተግበር፣
• በሁሉም የመንግሥት እርከኖች የሚገኙ የሴቶችን ውክልና ማጠናከር (የሥርዓተ ጾታ ኮታ ትግበራን ጨምሮ)፣
• ለሴቶች እጩዎች እና ለተመረጡ ተወካዮች በፖለቲካዊ ሂደቶች ውስጥ በብቃት እንዲሳተፉ ለማድረግ ሥልጠና እና ድጋፍ መስጠት፣
• በሕዝብ መረጃ ዘመቻዎች እና ትምህርታዊ ፕሮግራሞች የሴቶችን መብት እና የፖለቲካ ተሳትፎ ግንዛቤን ማሳደግ፣

በዓለም አቀፍ የሥርዓተ ጾታ ልዩነት መሠረት ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ በ2023 71.1 በመቶ የሥርዓተ ጾታ ልዩነትን በማግኘት 75ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች። ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር በ0.6 በመቶ መሻሻል አሳይታለች። ኢትዮጵያ ባለፉት 5 ዓመታት ገደማ በሴት ፕሬዚዳንት እየተመራች ትገኛለች። 41.3 በመቶ ሴት የፓርላማ አባላት እና 40.9 በመቶ ሴት ሚኒስትሮች ነበሩ። ይህ ውጤት በፖለቲካ ማጎልበት ላይ ያለውን የሥርዓተ ጾታ ልዩነት 43.1 በመቶ መቀየር ችሏል። ከዐሥር ዓመታት በፊት ከነበረው አኳያ ደግሞ ውጤቱን በሦስት እጥፍ ገደማ አሳድጓል። 25.4 በመቶ ከፍተኛ መኮንኖች እና 34.3 በመቶ የቴክኒክ የሥራ መደቦች በሴቶች የተያዙ ናቸው። እ.ኤ.አ በ2022 ሴቶችን ወደ አመራርነት ማሳደግ 3.27 በመቶ የጨመረ ሲሆን፣ በዚህም ሀገሪቱ በ74ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች። ይህም እ.ኤ.አ በ2021 ከነበረችበት 97ኛ ደረጃ ከፍተኛ መሻሻል አሳይታለች። የሴቶችን የፖለቲካ ተሳትፎ በተመለከተ ትምራን ባሰባሰበችው መረጃ መሠረት በፓርላማ ውስጥ 50 በመቶ ሴት ፖለቲከኞች እና ተወካዮች ውክልና አላቸው።

The Universal Periodic Review (UPR)

The Universal Periodic Review (UPR) is a unique process in which the human rights records of all 193 United Nations Member States are reviewed every five years. In the context of Ethiopia, the UPR has provided recommendations for the country to improve its human rights situation, particularly concerning women’s political participation.

The Universal Periodic Review (UPR) is a process that reviews the human rights records of all 193 United Nations Member States. The 3rd UPR cycle focused on Ethiopian women’s political participation. The recommendations made can be categorized into three areas: legal framework, political participation, and capacity building. Recommendations were made to strengthen the legal framework for women’s political participation in Ethiopia by adopting a comprehensive gender equality law and amending the constitution. Ethiopia has enacted affirmative action laws to enhance women’s representation in political institutions, such as the National Policy on Women and the Electoral Law. Despite significant efforts by the Ethiopian government to promote gender equality and women’s empowerment, Ethiopian women still face challenges in accessing and participating in political processes. The UPR process provides a platform to address these challenges and identify ways to improve women’s political participation in the country.

The legal framework in Ethiopia has undergone significant changes to promote and protect women’s rights in political processes. Ethiopia’s constitution mandates affirmative action measures to ensure women’s equal participation in decision-making bodies. The Election Proclamation requires political parties to ensure at least 30% of their candidates are women. Ethiopia has also enacted affirmative action laws to enhance women’s representation in political institutions. The country’s National Policy on Women aims to increase women’s participation in leadership and decision-making positions. Despite these efforts, women remain underrepresented in Ethiopian politics, holding only 50% of parliamentary seats. More needs to be done to ensure equal representation and promote gender equality in political structures and activities. Furthermore, The Organization of Civil Societies Proclamation No. 1113/2019 CSO Proclamation mandates that at least 30% of the board members of charities and NGOs must be women. In Ethiopia, women’s political participation is a crucial aspect of the country’s democratic development.

Recommendations were made to increase women’s participation in politics and ensure their voices are heard by establishing a quota system for women’s representation in political parties, parliaments, and local government bodies. Providing training and support for women candidates and elected representatives and encouraging political parties to actively promote gender equality and women’s participation in their structures and activities are also suggested. To improve women’s capacity to participate in political processes, recommendations were made in the areas of education, awareness-raising, and leadership development. Measures include ensuring equal access to education for girls, promoting gender-sensitive curricula in schools, and conducting awareness campaigns to challenge gender stereotypes. Training and mentoring programs for women leaders to enhance their skills and confidence are also recommended.

During the 3rd UPR cycle, several recommendations were made to improve women’s political participation in Ethiopia. These recommendations included:

• Ensuring that women have equal access to education and healthcare services, as these are essential for their empowerment and participation in political life.
• Adopting and implementing laws and policies that promote gender equality and women’s rights, such as the 1995 Constitution of the Federal Democratic Republic of Ethiopia, which guarantees equal rights for women and men.
• Strengthening the representation of women in decision-making bodies at all levels of government, including through the implementation of gender quotas.
• Providing training and support for women candidates and elected representatives to enable them to effectively participate in political processes.
• Increasing awareness of women’s rights and political participation through public information campaigns and educational programs.

As per global gender gap, Ethiopia ranks 75th, having closed 71.1% of the gender gap in 2023. Compared to the previous edition, it has improved by 0.6 percentage points. Ethiopia has had a woman president the past 5 years, along with 41.3% incumbent woman parliamentarians and 40.9% women ministers. These results in a closing 43.1% of the gender gap on the Political Empowerment almost triple its score since a decade back (14.6% in 2013). Only 25.4% of senior officers and 34.3% of technical positions are held by women. Advancement of women to leadership roles was 3.27 percent and ranked 74th in 2022. In 2021 Ethiopia ranked 97, it shows high improvement in 2022. As per the data collected by TIMRAN based on women political participation, the parliaments have 50 present representations by women politicians and representatives.

Share this post on

Share on facebook
Share on telegram
Share on whatsapp
Share on pinterest
Share on twitter
Share on linkedin
Share on skype
Share on print

Latest Posts