Timran

ሴቶችን በሚመለከት የኢትዮጵያ ምርጫ ሕግ ዳሰሳ

በኢትዮጵያ ምርጫ እና የሴቶች ተሳትፎን በሚመለከት የሕግ ማእቀፉ በዋናነት የሚመራው በ1987 ዓ.ም በወጣው የኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት ነው። ሕገ መንግሥቱ ለኹሉም ሰው በሕግ ፊት እኩልነትን የሚያረጋግጡ እና ጾታን መሠረት ያደረገ አድልኦ የሚከለክሉ ድንጋጌዎችን ይዟል፤ ይኽም በተለያዩ ፖሊሲዎች የጾታ እኩልነትንና የሴቶችን ተጠቃሚነት ለማሳደግ ያለመ ነው። በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 35 (1) ላይ ሴቶች በሕገ መንግሥት የተደነገጉትን መብቶች እና ጥበቃዎች ሲያገኙ ከወንዶች ጋር እኩል መብት እንዳላቸው ይገልጻል።

የኤፌዴሪ ሕገ መንግሥት ከመውጣቱ በፊት በ1985 ዓ.ም ሥራ ላይ የዋለው የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ፖሊሲ የሴቶችን ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ መብቶች ተቋማዊ ለማድረግ ጉልህ ሚና ይጫወታል። ብሔራዊ ፖሊሲው የሕዝብ ፖሊሲዎች ሥርዓተ ጾታ ተኮር መሆናቸውን ለማረጋገጥ በመንግሥት ተቋማት ውስጥ መዋቅሮችን በመፍጠር ላይ ያተኩራል። ከሴቶች መብት እና ማብቃት ጋር የተያያዙ አሳሳቢ ጉዳዮችን በመፍታት ይኽ ፖሊሲ በኢትዮጵያ ውስጥ ለወንዶችም ለሴቶችም ፍትሐዊ እድገትን ለማስፈን ያለመ ነው። ኢትዮጵያ በአራተኛው የዓለም ጉባኤ የቤጂንግ የድርጊት መድረክን ያለምንም ቅድመ ኹኔታ ደግፋለች። ሀገሪቱ በንኡስ ክልል እና በክልል ደረጃ በሰነዱ ዝግጅት ሂደት ላይ በንቃት ተሳትፋለች። ይኽ ድጋፍ ኢትዮጵያ የጾታ እኩልነትንና የሴቶችን መብት ከዓለም አቀፍ ደረጃዎች ጋር ለማጣጣም ያላትን ቁርጠኝነት ያሳያል። በኢትዮጵያ ውስጥ ከተተገበሩ ቁልፍ ስልቶች አንዱ የሥርዓተ ጾታ ጉዳዮችን በኹሉም የፖሊሲ እና የፕሮግራም ጣልቃ ገብነቶች ውስጥ ማካተት ነው። የሥርዓተ ጾታ አመለካከቶችን ወደ ተለያዩ ውጥኖች በማዋሐድ በልማት ላይ ያሉ ክፍተቶችን በማጥበብ በወንዶች እና በሴቶች ላይ በተለያዩ ዘርፎች እኩል እድሎችን ለማስተዋወቅ ያለመ ነው።

የኢትዮጵያ ምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ሥነ ምግባር ደንብ አዋጅ 1162/2011 አንቀጽ 74 (4) ማንኛውም የፖለቲካ ድርጅት የአመራር ቦታን ምርጫ ሲያካሂድ የሥርዓተ ጾታን ውክልና ግምት ውስጥ ማስገባት እንደሚኖርበት ይደነግጋል። አንቀጽ 100 ላይ ደግሞ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚያገኙት የገንዘብ ድጋፍ ሕጋዊ ተግባራትን እንዲያከናውኑ እና ግዴታቸውን እንዲወጡ ለማድረግ ሲኾን፣ በንኡስ አንቀጽ 2 (ሐ) እና (መ) በተቀመጡት መስፈርቶች መሠረት የገንዘብ ድጋፉ የሚሰጠው በእጩነት በቀረቡት ሴት እጩዎች ብዛት እና በፓርቲው የሴት አባላት ብዛት እና በአመራር ቦታ ላይ ባሉ ሴቶች ብዛት ላይ በመመሥረት ነው።

የኮታ ሥርዓት መተግበር ሴቶች በፓርላማ ውስጥ ያላቸውን ዝቅተኛ መቶኛ መቀመጫ በማስተካከል በፖለቲካ ውክልና ውስጥ ያለውን የሥርዓተ ጾታ ልዩነት ለመፍታት ይረዳል። ይኽ የነቃ እርምጃ የሴቶችን የፖለቲካ ተሳትፎ በታሪክ የተገደቡ አባታዊ ደንቦች እና የባሕል እንቅፋቶችን በመቋቋም ለሴቶች የተወሰኑ መቀመጫዎችን በመለየት ሴቶች በውሳኔ ሰጭ አካላት ውስጥ የመወከል ፍትሐዊ እድል እንዲኖራቸው ያደርጋል።

Overview of Ethiopian Election Law Regarding Women

In Ethiopia, the legal framework regarding elections and women’s participation is primarily governed by the FDRE 1994/5 Constitution. The Constitution contains provisions that guarantee equality before the law for all individuals and prohibit discrimination based on gender and various policies aimed at promoting gender equality and women’s empowerment. Article 35 (1) states: Women shall, in the enjoyment of rights and protections provided for by this Constitution, have equal rights with men.

The 1993 National Policy on Women, endorsed before the Constitution, also plays a significant role in institutionalizing the political, economic, and social rights of women. The Women’s Policy focuses on creating structures within government institutions to ensure that public policies are gender sensitive. By addressing critical concerns related to women’s rights and empowerment, this policy aims to promote equitable development for both men and women in Ethiopia.

Ethiopia endorsed the Beijing Platform for Action without reservation during the IV World Conference in 1995. The country actively participated in the preparatory process of the document at sub-regional and regional levels. This endorsement signifies Ethiopia’s commitment to advancing gender equality and women’s rights in line with international standards.

One of the key strategies employed in Ethiopia is mainstreaming gender considerations into all policy and program interventions. By integrating gender perspectives into various initiatives, the government aims to bridge gaps in development and promote equal opportunities for men and women across different sectors.

The Ethiopian Electoral, Political Parties Registration, and Election’s Code of Conduct Proclamation No. 1162/2019 Article 74 (4) states that any political party when conducting an election for a leadership position shall ensure gender representation consideration. Article 100 pinpoints parties will receive financial support and the amount a political party receives enables it to conduct legal operations and carry out its obligations, the Board shall seek approval of the FDRE House of Peoples’ Representatives, government’s support to parties, based on the criteria established under sub-article2 (c) and (d). The financial support for the parties will be given based on the number of female candidates it nominates, the number of female members of the party, and the number of females in leadership positions.

A quota system would help address the existing gender disparities in political representation by mandating a minimum percentage of seats for women in parliament. This proactive measure can help counteract the patriarchal norms and cultural barriers that have historically limited women’s participation in politics. By setting aside a certain number of seats for women, the quota system ensures that women have a fair chance to be represented in decision-making bodies.

Share this post on

Share on facebook
Share on telegram
Share on whatsapp
Share on pinterest
Share on twitter
Share on linkedin
Share on skype
Share on print

Latest Posts