Timran

ሴቶችን በፖለቲካ ውስጥ ማካተት ለጾታ እኩልነት

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በአመራር ቦታዎች በተለይም ሴቶች እኩል ውክልና ባላገኙባቸው አገሮች የሥርዓተ-ጾታ እኩልነት ጥሪ እየጨመረ መጥቷል። ከእነዚህ አገሮች አንዷ ኢትዮጵያ ነች፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሴት ፕሬዚዳንት የመኖሯ ተስፋ በአገሪቱ ላይ በርካታ አዎንታዊ ተጽእኖዎች ይኖሩታል።

በፖለቲካ አመራር ቦታዎች ላይ የሴቶችን ውክልና ለማሳደግ ዓለም አቀፍ እንቅስቃሴ እያደገ መጥቷል። ይህ የሥርዓተ-ጾታ እኩልነት ግፊት በርካታ ሴቶች የፕሬዚዳንትነትን መንበር ጨምሮ ከፍተኛ የፖለቲካ ሥልጣን እንዲይዙ አድርጓል። በኢትዮጵያ ሳህለወርቅ ዘውዴ ከሚያዚያ 2010 ዓ.ም ጀምሮ ፕሬዚዳንት ሆነው መሾማቸው በአገሪቱ ታሪክ ውስጥ ትልቅ ምእራፍ ነበር።

በኢትዮጵያ ውስጥ የፕሬዚዳንትነት ሥልጣን በሴት መያዙ ከሚያስገኛቸው አዎንታዊ ውጤቶች አንዱ የሴቶች በፖለቲካ አመራር ውስጥ ያለው ውክልና መጨመር ነው። ይህ ውክልና ለተቀረው ሕዝብ በተለይም ወጣት ልጆች እና ሴቶች የሥልጣን ቦታዎችንና የውሳኔ ሰጭነት ቦታዎች ለመያዝ እንዲያስቡ ያደርጋል። ሴቶች በፖለቲካ እና ወደ አመራርነት እንዲመጡ አርአያነት አለው። በኢትዮጵያ ውስጥ ሴት ፕሬዚዳንት መኖሩ ከሚታዩት በጎ ነገሮች አንዱ የተሻለ የሴቶች ውክልና እና ሴቶችን በፖለቲካ ዘርፍ ማካተት መቻል ነው።

ሴቶች ከፍተኛውን የፖለቲካ ሥልጣን መያዛቸው ለአገሪቱ እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከት እንደሚችሉ ያሳያል። ይህም የተዛቡ የሥርዓተ-ጾታ አመለካከቶችን ለመቀነስ እና የበለጠ ሁሉን አቀፍ የፖለቲካ ምኅዳር ለመፍጠር ይረዳል። በተጨማሪም ለሥርዓተ-ጾታ ትኩረት በሚሰጡ ፖሊሲዎች ላይ ለሴቶች ቅድሚያ ለመስጠት እንዲቻል ያደርጋል።

በኢትዮጵያ ውስጥ ሴቶች ፕሬዚዳንትነት ጨምሮ በሥራ አስፈጻሚው ውስጥ ያላቸው ውክልና መጨመር በአገር ደረጃ ለረጅም ጊዜ የቆዩ የሥርዓተ-ጾታ ልዩነቶችን ለመቀነስ መንገድ ይጠርጋል። ይህ በትምህርት፣ በጤና እንክብካቤ እና በሥራ ስምሪት የሥርዓተ-ጾታ እኩልነትን የሚያሳድጉ ፖሊሲዎችን ለመተግበር ብሎም የቤት ውስጥ ጥቃት እና የሴት ልጅ ግርዛትን የመሳሰሉ ጉዳዮችን ለመግታት ያግዛል።

የሳህለወርቅ ዘውዴ የፕሬዚዳንትነት ዘመን በዓለም አቀፍ ትብብር እና ዲፕሎማሲ ላይ አዲስ ትኩረት አምጥቷል፤ ኢትዮጵያ በአህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ ንቁ ሚና እንድትጫወት አድርጓል። ፕሬዚዳንቷ በተለይ በአፍሪካ ቀንድ ሰላም እና መረጋጋትን ለማስፈን ባደረጉት ጥረት በቀጣናው ተዋናዮች መካከል መግባባት ለመፍጠር እና በተጋላጭ አካላት መካከል ውይይቶችን ለማመቻቸት ሠርተዋል።

ኢትዮጵያ ሴት ፕሬዚዳንት ያላት በመሆኑ በረጅም ጊዜ የሚጠቅም አጋርነትንና ጥምረትን በመፍጠር ከሌሎች ሀገራት ጋር ድልድይ ለመሥራት ያስችላታል። ይህም የውጭ እርዳታን፣ ኢንቨስትመንቶችንና ለአገሪቱ የልማት ጥረቶች ድጋፍ እንዲመጣ ያደርጋል። የሴት ፕሬዚዳንት መኖር በአንድ ሀገር ውስጥ የተሻለ ማኅበራዊ እና ፖለቲካዊ መረጋጋት መኖር አስተዋጽኦ ያደርጋል። የሳህለ ወርቅ ዘውዴ የፕሬዚዳንትነት አመራር በአገር ደረጃ የሚታዩ ልዩነቶች በውይይት እና መግባባት እንዲፈቱ ማድረግ ላይ ያተኮረ ነው።

ኢትዮጵያ ያጋጠሟትን ውስብስብ ፈተናዎች እየዳሰሰች ባለችበት ወቅት፣ እነዚህን ድሎች ማጎልበት እና የሴቶች ድምፅ እና አመለካከቶች በሁሉም የፖለቲካ ሕይወት ዘርፎች ውክልና እና ዋጋ እንዲኖራቸው ማድረግ አስፈላጊ ነው። በሚቀጥሉት ዓመታት በኢትዮጵያ ውስጥ ሴት ፕሬዚዳንት መኖሩ የተለያዩ ገንቢ ውጤቶችን ማለትም የተሻሻሉ ውክልና እና ማካተት፣ የሴቶችን መብት ማሳደግ እና ማብቃት፣ የኢኮኖሚ እድገትን ማጠናከር፣ የዓለም አቀፍ ግንኙነቶችን ማጠናከር፣ ግልጽነት እና ተጠያቂነት መጨመርን ይጨምራል። እነዚህ ሊሆኑ የሚችሉ ጥቅማ ጥቅሞች በኢትዮጵያ ውስጥ የሴት ፕሬዚዳንት ተስፋን አመርቂ እና ተስፋ ሰጭ ያደርገዋል።

በኢትዮጵያ ውስጥ እያደገ የመጣውን ሴቶችን ወደ ፖለቲካ የማምጣት አስፈላጊነት ማስፋት ያስፈልጋል። ምክንያቱም ሴቶችን በፖለቲካ ውስጥ ማካተት የሥርዓተ ጾታ እኩልነትን ከማስፈን ባለፈ የውሳኔ አሰጣጥ ሂደቶችን ለማጎልበት እና መጪውን ትውልድ ለማነሣሣት ወሳኝ ነው። ስለሆነም መንግሥት በፖለቲካዊ አመራር ውስጥ የሴቶችን ተሳትፎ በንቃት በመደገፍ ሰላም እና መረጋጋት የሰፈነባት አገር ለመገንባት እና ሁሉንም ያሳተፈ ዴሞክራሲ እንዲኖር ማድረግ ይጠበቅበታል።

Inclusion of women in politics for gender equality

In recent years, there has been a growing call for gender equality in leadership positions, especially in countries where women are not equally represented. One of these countries is Ethiopia, recently the prospect of having a female president will have many positive effects on the country.

There has been a growing global movement to increase the representation of women in political leadership positions. This push for gender equality has resulted in a number of women assuming top political offices, including the presidency. In Ethiopia, the appointment of Sahle-Work Zewde as the President in April 2018 marked a significant milestone for the country.

One of the most significant positive impact of having a woman as President in Ethiopia is increased representation of women in political leadership. This representation sends a powerful message to the rest of the population, particularly young girls and women that they can aspire to hold positions of authority and decision-making places. Having women president has provided a positive example for women and girls to follow, inspiring them to pursue careers in politics and leadership. One of the most apparent benefits of having a woman president in Ethiopia would be the improved representation and inclusion of women in the political sphere. A female president would serve as a role model for women and girls across the country, demonstrating that women can hold the highest political office and contribute significantly to the nation’s development. This will help reduce gender stereotypes and create a more inclusive political environment. It also allows women to be prioritized in gender sensitive policies.

Having a woman as President can lead to a greater focus on gender-sensitive policies and priorities. Sahle-Work Zewde’s presidency has been marked by a renewed emphasis on addressing gender inequality and promoting women’s empowerment. This includes initiatives to improve access to education, healthcare, and economic opportunities for women and girls, as well as efforts to combat gender-based violence and promote gender equality in all sectors of society. A woman president in Ethiopia would likely prioritize women’s rights and empowerment, addressing long-standing gender inequalities in the country. This could include implementing policies to promote gender equality in education, healthcare, and employment, as well as addressing issues such as domestic violence and female genital mutilation. By focusing on these areas, a female president could help to create a more equitable society in which women have the same opportunities as men.

Increasing women’s representation in the executive branch, including the presidency, in Ethiopia paves the way for reducing long-standing gender disparities at the national level. This will help implement policies that promote gender equality in education, health care and employment, as well as curb issues such as domestic violence and female genital mutilation.

Sahlework Zewde’s presidency brought a new focus on international cooperation and diplomacy; it has made Ethiopia play an active role in continental and global affairs. The President has worked to create understanding among actors in the Horn region and to facilitate discussions between the vulnerable parties, especially she is well-known in her efforts to achieve peace and stability in the Horn of Africa.

Since Ethiopia has a female president, it enables to build bridges with other countries by creating long-term beneficial partnerships and alliances. This brought foreign aid, investments and support for the country’s development efforts. Having a female president contributes to better social and political stability in a country. Sahle Work Zewde’s presidency is focused on solving national differences through dialogue and understanding.

Ethiopia is navigating the complex challenges it faces, so it is important to build on the gains and ensure that women’s voices and perspectives are represented and valued in all areas of political life. In the years to come, having a female president in Ethiopia will have a range of constructive outcomes, including improved representation and inclusion, increased women’s rights and empowerment, enhanced economic growth, strengthened international relations, increased transparency and accountability. These potential benefits make the prospect of a female president in Ethiopia attractive and promising.

It is significant to expand the importance of bringing women into political position in Ethiopia. Because the inclusion of women in politics is not only important for achieving gender equality, but also for enhancing decision-making processes and motivating the next generation. Therefore, the government should actively support women’s participation in political leadership to build a peaceful and stable country as well as ensure an inclusive democracy.

Share this post on

Share on facebook
Share on telegram
Share on whatsapp
Share on pinterest
Share on twitter
Share on linkedin
Share on skype
Share on print

Latest Posts