Timran

ሴቶች በሽግግር ፍትሕ አተገባበር ውስጥ የሚኖራቸው ትርጉም ያለው ተሳትፎ ዓለም አቀፍ ማእቀፍ

ባለፉት 20 ዓመታት በላይ በዓለም አቀፍ የሰላም እና ደኅንነት ሕጎች ውስጥ ሴቶች በሽግግር ፍትሕ አተገባበር ውስጥ የሚኖራቸው ትርጉም ያለው ተሳትፎ መሠረታዊ ቅድመ ኹኔታ ተደርጎ ሲተገበር ቆይቷል። ከእነዚህ ዓለም አቀፍ ሕጎች መካከል ዋነኞቹ:-
o የተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ውሳኔ ሐሳብ ቁጥር 1325 ላይ የሴቶች ሰላም እና ደኅንነት (2000) በሚል ርእስ የተቀመጠው ውሳኔ በቀዳሚነት የሚታይ ሲኾን፣ ሴቶች በዋናነት በሁሉም የሰላም እና ደኅንነት ሥራዎች እና ማስተዋወቅ ውስጥ መገኘት፣ የሴቶች እኩል ተሳትፎ እና ሙሉ አስተዋጽኦ እንዲኖር ብሎም የእነርሱ የውሳኔ ሰጭነት ሚና እንዲጨምር እንደሚያደርግ ያትታል።
o የሽግግር ፍትሕን አስመልክቶ የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ መመሪያ (2010) መርህ 4 ሁለተኛው ዓለም አቀፍ ሕግ ሲኾን፣ በሽግግር ፍትሕ ሂደቶች እና ስልቶች ውስጥ የሴቶችን መብቶች ማረጋገጥ ይመለከታል።
በዓለም አቀፍ የሴቶች የሰላም እና ደኅንነት ፖሊሲ ማእቀፍ ላይ እንደተገለጸው ሴቶች በሽግግር ፍትሕ ውስጥ ትርጉም ባለው መልኩ መሳተፋቸው ቁልፍ ጉዳይ ነው። እነዚኽም:-
• የሴቶች እኩል ተሳትፎ መሠረታዊ የሕግ መብት በመሆኑ፣
• የሴቶች ትርጉም ያለው ተሳትፎ አግላይ የሥልጣን መዋቅሮችን ስለሚገዳደር፣
• በሽግግር ፍትሕ ውስጥ ሴቶች ባለቤት እንጂ ተከታይ ባለመሆናቸው፣
• የሴቶች ትርጉም ያለው ተሳትፎ መኖር በሁሉም ዘርፎች እንዲሳተፉ ስለሚያስገድድ እና
• የሴቶች ትርጉም ያለው ተሳትፎ የአፈጻጸም ውጤታማነትን የሚያሻሽል በመኾኑ ነው።
በሽግግር ፍትሕ ውስጥ የሴቶች ትርጉም ያለው ተሳትፎ ገጽታ
በሽግግር ፍትሕ ሁሉም ደረጃዎች እና ኹኔታዎች ውስጥ ሴቶች ትርጉም ባለው መልኩ በብዛት መሳተፋቸው የግድ አስፈላጊ ነው። ነገር ግን የሴቶች ትርጉም ያለው ተሳትፎ ማለት የሴቶች ቁጥር መብዛት አይደለም፤ ይልቁንም የሽግግር ፍትሕ ሂደቶች እና ውጤቶች ላይ የሴቶችን ተሳትፎ ጥራት ባለው እና ውጤታማ በሆነ መልኩ ማረጋገጥ ማለት ነው።
በሽግግር ፍትሕ ውስጥ የሴቶች ትርጉም ያለው ተሳትፎ ምንነት
የሴቶች ትርጉም ያለው ተሳትፎ የበርካታ ጉዳዮች ድምር እና ብዝኀ ማንነት ያላቸው ሴቶች ሲካተቱ የሚታይ ውጤት ነው።
• ሴቶች ወደ መዋቅር፣ አሠራሮች እና ሥልጣን በነፃነት፣ ያለመሰናክል እና ለደኅንነታቸው ሳይሰጉ የመምጣት ችሎታ አላቸው።
• ሴቶች በመዋቅር፣ አሠራሮች እና ሥልጣን ላይ ሲቀመጡ በቀጥታ የመምራት፣ ተፅዕኖ የመፍጠር እና ውሳኔ የመስጠት እድል ያገኛሉ።
• ሴቶች ወደ መዋቅር፣ አሠራሮች እና ሥልጣን ሲመጡ በራስ ማንነት፣ በዕውቀት እና በራስ መተማመን የጾታቸውን ፍላጎቶች፣ እሴቶች እና ልምዶችን ውጤታማ በኾነ መንገድ መወከል ይችላሉ።
• ሴቶች ቡድናቸውን በማንቀሳቀስ ማስረጃ በመሰብሰብ፣ አጀንዳ በመቅረፅ፣ ጥምረት በመመሥረት እና በጋራ ስትራቴጂዎችን በመተግበር ለውጥ ለማምጣት ይችላሉ።
• ሴቶች መዋቅር፣ አሠራሮች እና ሥልጣን ላይ ሲወጡ ብዝኀ ማንነት ያላቸው ሴቶችን ብሎም የሰፊው ኅብረተሰብ ፍላጎቶች፣ እሴቶች እና ልምዶች የሚያንጸባርቁ ውሳኔ የተሰጠባቸው ጉዳዮች ውጤቶችን መቀየር የሚያስችል ተፅዕኖ ማሳረፍ ይችላሉ።
ብዝኀ ማንነት ያላቸው ሴቶችን የቁጥር ተሳትፎ መጨመር ብሎም ሚናቸውን በአግባቡ እንዲወጡ እና ተፅዕኖ ማሳደር እንዲችሉ ምቹ ኹኔታ መፍጠር ለሴቶች ትርጉም ያለው ተሳትፎ ወሳኝ ጉዳዮች ናቸው። (www.undp.org)

Share this post on

Share on facebook
Share on telegram
Share on whatsapp
Share on pinterest
Share on twitter
Share on linkedin
Share on skype
Share on print

Latest Posts

Archives


Categories