የሽግግር ፍትሕ ውጤታማ እንዲኾን ሴቶች በኹሉም ደረጃ እና ኹኔታ ውስጥ ትርጉም ያለው ተሳትፎ እንዲኖራቸው ማድረግ ያስፈልጋል።
በአጭሩ ሴቶች በሂደቱ ውስጥ መኖራቸው የግድ ነው። ነገር ግን ሴቶች ትርጉም ያለው ተሳትፎ ሊኖራቸው ይገባል ማለት አኀዛዊ ውክልና ሊኖራቸው ይገባል ብቻ ማለት ሳይኾን፣ የሽግግር ፍትሕ ሂደቶች እና ውጤቶች ላይ ተፅዕኖ ማድረግ የሚችል ጥራት እና ብቃት ያለው ሚና ሊኖራቸው ይገባል ማለት ነው።
ስለኾነም የሴቶች ትርጉም ያለው ተሳትፎ ብያኔ ከቁጥር ጨዋታ ባለፈ ሊታይ ያስፈልጋል። ይኽንን እውን ማድረግ ደግሞ ነባራዊው ዐውድ ላይ የተመሠረተ ይኾናል። የሴቶች ትርጉም ያለው ተሳትፎ የበርካታ ጉዳዮች መገጣጠም እና የተለያየ መሠረት ያላቸው ሴቶች ሲወከሉ የሚገኝ ውጤት ነው።
ለዚኽ ኹኔታ መሳካት አስፈላጊ ከኾኑ ጉዳዮች መካከል በሽግግር ፍትሕ ውስጥ የሚወከሉ ሴቶች ወደ ሂደቱ ለመግባት የሚያስችል መደላድል፣ ስልት ብሎም ያለ ውጣ ውረድ እና ያለ ፍርሃት ሊሠሩ የሚችሉበት ኹኔታ መኖር፣
በተጨባጭ የሚታዩት መደላድሎች፣ ስልቶች እና ኹኔታዎች ሴቶች በቀጥታ መረጃ መስጠት፣ ተፅዕኖ ማሳደር እና ውሳኔ መወሰን የሚችሉበትን እድል መፍጠር፣
ሴቶች ራሳቸውንና ብዝኀነት ያላቸው መሰሎቻቸውን ፍላጎቶች፣ እሴቶች እና ልምዶች በአግባቡ መወከል እንዲችሉ ራሳቸውን መግለጽ፣ ዕውቀት እና በራስ መተማመን ያላቸው መኾን፣
መረጃ በመሰብሰብ፣ ተጨባጭ አጀንዳ በመያዝ፣ ጥምረት በመፍጠር እና ለውጥ ለማምጣት በትብብር መንቀሳቀስ የሚያስችል ስትራቴጂ መቀየስ እና ብዝኀነት ያላቸው ሴቶችን ብሎም የሰፊውን ኅብረተሰብ ፍላጎቶች፣
እሴቶች እና ልምዶች በመያዝ ውሳኔ የተሰጠባቸውን ውጤቶች መለወጥ የሚያስችል ተፅዕኖ ማሳደር የሚችሉ መኾን ይገኙበታል።
በመኾኑም ብዝኀነት ያላቸው ሴቶችን ተሳትፎ መጨመር ብሎም ሚናቸውን ጥራት ያለው እና ተፅዕኖ ማሳደር እንዲችል ማድረግ ሴቶች ትርጉም ያለው ተሳትፎ ማድረግ እንዲችሉ አስፈላጊ ጉዳዮች ናቸው።
Defining women’s meaningful participation in transitional justice
The ‘quantity’ of women at all levels and in all elements of transitional justice is a necessary part of meaningful participation—clearly, women must be present. However, women’s meaningful participation is not simply about the quantity of women, but about the quality and effectiveness of their role to influence transitional justice processes and outcomes.
Women’s meaningful participation, therefore, needs a definition beyond the number game. How this is achieved in any given context will depend greatly on that context.
Definition for women’s meaningful participation in transitional justice:
Meaningful women’s participation involves the convergence of several elements and manifests when women from diverse backgrounds:
Have the ability to enter settings, mechanisms and positions of power freely and unhindered and without fear for their safety;
Are present in settings, mechanisms and positions of power so that they can directly seize opportunities to inform, influence and make decisions;
Possess self-efficacy, knowledge and confidence to effectively represent their whole and diverse intersectional range of ‘gendered’ interests, values and experiences;
Deploy their agency by gathering evidence, substantively setting agendas, building coalitions and collaboratively mobilizing strategies to impel change; and
Exert influence that alters decision-making outcomes to better reflect diverse women’s interests, values and experiences and, therefore, also those of the wider society.
Increasing the numbers (i.e. numeric or descriptive participation) of a diverse cross-section of women and enabling the conditions by which the quality and impact of their roles (i.e. the substantive representation of their gendered interests in decision-making) can be deepened are vital twin-tracks of meaningful inclusion.
Taken from UN WOMEN: Women’s Meaningful Participation in Transitional Justice-March 2022

የትምራን ጊዜያዊ ሥራ አስፈጻሚ በሲቪክ ማኅበራት ብሔራዊ የጥናት ጉባኤ ላይ ጥናታዊ ጽሑፍ አቀረቡ
የትምራን ጊዜያዊ ሥራ አስፈጻሚ ማኅደር ዳዲ በአገር አቀፍ ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ በመካሄድ ላይ በሚገኘው የሲቪክ