ትምራን ሴቶች በሀገሪቱ የፖለቲካ እና የሕዝብ አስተዳደር እንቅስቃሴዎች ውስጥ የሴቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎ ለማጎልበት ታስባ የተጠነሰሰች ሀገር በቀል የሲቪክ ማኅበር ናት።
በዚህም መሠረት ከማናቸውም ወገንተኝነት ነፃ በመሆን የተለያየ የፖለቲካ አመለካከት የሚያራምዱ ሴቶች በግልም ሆነ በፓርቲ አባልነት የነቃ ፖለቲካዊ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ታበረታታለች።
ትምራን በኢፌዴሪ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን መጋቢት 2012 ዓ.ም ውስጥ ተመዝግባ ላለፉት ሦስት ዓመታት በመንቀሳቀስ ላይ ትገኛለች።
የኢፌዴሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መጋቢት 26 ቀን 2015 ዓ.ም ባካሄደው 13ኛ መደበኛ ጉባኤ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 81 (2) መሠረት የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት እና ምክትል ፕሬዚዳንት ሹመትን አጽድቋል።
በዚህም መሠረት ወ/ሮ ሌሊሴ ደሳለኝ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት እንዲሁም ወ/ሮ ዘሃራ ዑመር ዓሊ ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው በምክር ቤቱ ተሹመዋል።
ትምራን በከፍተኛ የዳኝነት ሥልጣን እርከን ላይ ለተሾሙ ሴቶች እንኳን ደስ አላችኹ ማለት ትፈልጋለች።
ትምራን ሴቶች በየትኛውም የሀገሪቱ የውሳኔ ሰጭነት ሚና ወደፊት መምጣታቸው የሰከነ እና ውጤታማ አመራር እንዲኖር ጉልህ አስተዋጽኦ አለው የሚል እምነት አላት።
በመሆኑም ትምራን መሰል ፖለቲካዊ ውሳኔዎችን በአዎንታዊነት የምትቀበል እና አድናቆት የምትቸረው ሲሆን፣ ለተሿሚ ሴቶች መልካም የሥራ ጊዜ እንዲሆንላቸው ትመኛለች።
Bringing women into the nation’s decision-making role has the advantage to get a tranquil and effective leadership
TIMRAN emerged as a local nonpartisan civil society organization dedicated to advancing women’s participation in politics and public decision-making in Ethiopia regardless of their political opinion or party affiliation.
TIMRAN was registered by the Authority of Civil Societies Organization (ACSO) in March 2020 and worked for the last three years on the advancement of women’s political participation and leadership.
On April 04, 2023, the FDRE House of Peoples Representatives conducted its 13th regular meeting and nominated a female Federal High Court President and Vice President according to the constitution, Article 81 (2) of the constitution.
Accordingly, Mrs. Lelise Deslaegn was assigned to be the Federal High Court President, and Mrs. Zahara Oumer Ali was assigned the Vice Presidency by the parliament.
TIMRAN congratulates the women appointed to the higher judiciary positions.
TIMRAN believes bringing women into the nation’s decision-making roles has the advantage to get a tranquil and effective leadership in the country.
Thus, TIMRAN promotes such political decisions and has an admiration for the decision. We wish good luck to the appointed women.