በጥምረት ለሴቶች ድምፅ በሀገራዊ ምክክር የተዘጋጀ “በሀገራዊ ምክክር ውስጥ የሴቶች ትርጉም ያለው ተሳትፎ እና የባለድርሻ አካላት ሚና” በሚል ጭብጥ የውይይት መድረክ ግንቦት 07 ቀን 2015 ዓ.ም ላይ በአዲስ አበባ ከተማ ተካሄደ።
የጥምረት ለሴቶች ድምፅ በሀገራዊ ምክከር መድረክ የመርሐ ግብር ባለሞያ የሆኑት ሰላም ተስፋዬ ተሳታፊዎቹን እንኳን ደኅና መጣችኹ ካሉ በኋላ የጥምረቱን ዓላማ እና እያከናወናቸው ያሉ ተግባራትን አስተዋውቀዋል።
ጥምረቱ በሀገራዊ ምክክር ውስጥ የሴቶችን ትርጉም ያለው ተሳትፎ ለማረጋገጥ በ22 ድርጅቶች ከአንድ ዓመት በፊት የተቋቋመ መኾኑን ጠቅሰው፣ በአኹኑ ወቅት ከ50 በላይ አባል ድርጅቶች እንዳሉት ገልጸዋል።
በመርሐ ግብሩ የሀገራዊ ምክክር ምንነት፣ በሀገራዊ ምክክሩ ውስጥ የሴቶች ትርጉም ያለው ተሳትፎ እና በሀገራዊ ምክክር ሂደት ውስጥ የሌሎች ባለድርሻ አካላት ሚና የሚሉ ጉዳዮች ላይ ውይይት ይደረጋል።
የውይይት መድረኩ የጥምረት ለሴቶች ድምፅ በሀገራዊ ምክክር ጽ/ቤት በኾነችው ትምራን እና የጥምረቱ አባል በኾነው የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኀን ሴቶች ማኅበር ትብብር ከዩኤስኤይድ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ የተዘጋጀ ነው።
A panel discussion on the theme “Meaningful Participation of Women in the National Dialogue and the Roles of Other Stakeholders” underway
A panel discussion on the theme “Meaningful Participation of Women in the National Dialogue and the Roles of Other Stakeholders” organized by the Coalition for Women’s Voice in the National Dialogue underway on May 15, 2023, in Addis Ababa.
Selam Tesfaye, a Program Officer at the Coalition for Women’s Voice in the National Dialogue (CWVND), welcomed the participants and briefed them about the objective and activities of the Coalition.
She said the CWVND was established to ensure women’s meaningful participation in the National Dialogue by 22 CSOs a year ago and now it has more than 50 member organizations.
The panel discussion raises issues about the definition of national dialogue, the meaningful participation of women in the national dialogue, and the roles of other stakeholders in the national dialogue.
The panel discussion is facilitated by the secretariat office of the Coalition for Women’s Voice in the National Dialogue, TIMRAN, in collaboration with the CWVND member, Ethiopia Media Women Association funded by USAID.