በትምራን አዘጋጅነት ለኢትዮጵያ ሴት ፖለቲካ ፓርቲ አባላት ጥምረት ከየካቲት 28 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በመሰጠት ላይ የሚገኘው የፖለቲካ ተግባቦት እና የምርጫ ቅስቀሳ ዘመቻ ክሂሎት ሥልጠና ቀጥሏል።
በሁለተኛ እና ሦስተኛ ቀን ውሎ ፖለቲካዊ የምርጫ ቅስቀሳ ዘመቻ ተግባቦት ጋር በተያያዘ መራጮችን የማሳመን ፖለቲካ ቅስቀሳ ዘመቻ፣ ዕጩ መራጮችን የማሳመን ሂደቶች እና ብልሃቶች እንዲሁም የፖለቲካ ትረካዊ የምርጫ ቅስቀሳ የማሳመን ስልት እና የፖለቲካዊ ተግባቦት የማሳመን አተገባበር በሚሉ ርእሰ ጉዳዮች ሥልጠናው እየተሰጠ ይገኛል።
ከሲቪክ ማኅበራት ድጋፍ ፕሮግራም 2 በተገኘ የገንዘብ እገዛ እየተሰጠ ያለው ሥልጠና በነገው ዕለት ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።