Timran

በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ለሴቶች አዎንታዊ እርምጃ እና የኮታ ሥርዓት መኖር አስፈላጊነት

በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ለሴቶች አዎንታዊ እርምጃ እና የኮታ ሥርዓት መኖር የሥርዓተ-ጾታ አድልኦን ለመቅረፍ እና ሴቶች በውሳኔ አሰጣጥ ሂደቶች ውስጥ ያላቸውን ተሳትፎ ለማሳደግ ያለመ ጉልህ ተነሣሽነት ነው። ኮታዎች በሕግ አውጭ አካላት ውስጥ ለሴቶች የተከለሉ መቀመጫዎች ዝቅተኛ ገደብ ወይም መቶኛ እንዲኖር እድል ይሰጣሉ። እነዚህ ኮታዎች በፖለቲካ ተቋማት ውስጥ የወንዶች እና የሴቶችን ሚዛናዊ ውክልና ለማረጋገጥ በማሰብ በሕግ የተደነገጉ ወይም በፈቃደኝነት የተመሠረቱ ሊሆኑ ይችላሉ።

የኢትዮጵያ መንግሥት ሴቶች በፖለቲካዊ ዘርፍ እኩል ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ የተለያዩ ፖሊሲዎችንና ስትራቴጂዎችን ተግባራዊ አድርጓል። እነዚህ ጥረቶች ሴቶችን በማብቃት፣ ውክልናቸውን በማሳደግ እና የበለጠ አሳታፊ አስተዳደር እንዲኖር አስተዋጽኦ ለማድረግ ወሳኝ ናቸው።

አዎንታዊ እርምጃ እና የኮታ ሥርዓት እርምጃዎች በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ በሴቶች ተሳትፎ ላይ ጉልህ ተፅዕኖ አሳድረዋል። እነዚህ ውጥኖች በተለያዩ የመንግሥት እርከኖች ውስጥ የፖለቲካ ሥልጣን የሚይዙ ሴቶች ቁጥር እንዲጨምር አድርጓል። በፓርላማ እና በአካባቢ ምክር ቤቶች ለሴቶች የተያዙ መቀመጫዎችን በማዘጋጀት በፖለቲካ ውክልና ላይ ያለውን የሥርዓተ ጾታ አድልኦ ለማቃለል ረድቷል።

አዎንታዊ እርምጃ እና በኮታ ሥርዓት የተገኘው እድገት እንዳለ ሆኖ፣ አሁንም በፖለቲካ ውስጥ ሙሉ የጾታ እኩልነትን የሚያደናቅፉ ተግዳሮቶች አሉ። ሥር የሰደዱ ባሕላዊ ልማዶች፣ የሀብቶች አቅርቦት ውስንነት እና ኅብረተሰቡ ከሴቶች በኩል የላቀ አፈጻጸም ጥበቃ መኖሩ ሴቶች በፖለቲካ ውስጥ ባላቸው ንቁ ተሳትፎ ላይ እንቅፋት መፍጠራቸውን ቀጥለዋል። በተጨማሪም በአመራርነት ሚና ውስጥ በሴቶች ላይ የሚሰነዘሩ አመለካከቶች እና አድሎአዊ ድርጊቶች አሁንም ቀጥለዋል፣ ይህም የፖለቲካ መብቶቻቸውን በተሟላ መልኩ ለመጠቀም ፈታኝ ያደርገዋል።

እ.አ.አ 2021 ላይ የኢትዮጵያ ሴቶች ማኅበራት ቅንጅት ሲቪክ ማኅበር እና በኢፌዴሪ የሴቶች፣ ሕፃናት እና ወጣቶች ሚኒስቴር ትብብር የወጣ ጥናት በፖለቲካ ውስጥ የሴቶች ተሳትፎ እና ውሳኔ ሰጭነት ዝቅተኛ መኾኑን ያመላከተ ሲኾን፣ የሴቶችን የፖለቲካ እና የሕዝብ ተሳትፎ በየደረጃው ለማሳደግ አዳዲስ ኮታዎችንና ሌሎች አዎንታዊ እርምጃዎችን እንዲወሰድ ጠቁሟል።

በፖለቲካ ውስጥ የሴቶችን አዎንታዊ ተግባር እና የኮታ ሥርዓት የበለጠ ለማሳደግ ቀጣይነት ያለው ቅስቀሳ፣ የግንዛቤ ማስጨበጫ ዘመቻዎች እና የአቅም ግንባታ መርሐ ግብሮች ያስፈልጋሉ። ለሴት ፖለቲከኞች የድጋፍ ትስስሮችን ማጠናከር፣ የማማከር መርሐ ግብሮችን መተግበር እና በፖለቲካ ተቋማት ውስጥ ያሉ መዋቅራዊ ማነቆዎችን መፍታት የላቀ የጾታ እኩልነትን ለማምጣት ወሳኝ እርምጃዎች ናቸው።

በፖለቲካ ውስጥ ለሴቶች የሚሰጥ አዎንታዊ እርምጃ እና የኮታ ሥርዓት የጾታ እኩልነትን በማጎልበት እና ሴቶች በውሳኔ አሰጣጥ ሂደት ውስጥ ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ በማብቃት ረገድ ትልቅ ሚና ይጫወታል። ትንሽ ለውጥ እየታየ ቢሆንም ያሉትን ተግዳሮቶች ለመቅረፍ እና የኢትዮጵያን ኅብረተሰብ ብዝኀነት የሚያንፀባርቅ የፖለቲካ ምኅዳር ለመፍጠር ቀጣይነት ያለው ጥረት አስፈላጊ ነው።

The need of affirmative action and quota system for women in Ethiopian politics

Affirmative action and quota system in the Ethiopia political system for women has been a significant initiative aimed at addressing gender inequality and promoting women’s participation in decision-making processes. Quotas establish a minimum threshold or percentage of seats reserved for women in legislative bodies. These quotas can be either legislated or voluntary, aiming to ensure a more balanced representation of men and women in political institutions.

The government of Ethiopia has implemented various policies and strategies to ensure equal opportunities for women in political spheres. These efforts are crucial to empower women, enhance their representation, and ultimately contribute to more inclusive governance.

Affirmative action and quota system measures have had a notable impact on women’s participation in Ethiopian political system. These initiatives have led to an increase in the number of women holding political positions at different levels of government. By providing reserved seats for women in parliament and local councils, affirmative action and quota system has helped bridge the gender gap in political representation.

Despite the progress made through affirmative action and quota system, there are still challenges that hinder full gender equality in politics. Deep-rooted cultural norms, limited access to resources, and societal expectations continue to pose barriers to women’s active involvement in politics. Additionally, stereotypes and biases against women in leadership roles persist, making it challenging for them to fully exercise their political rights.

A 2021 report by Network of Ethiopian Women Association (NEWA) and Ministry of Women, Children and Youths (MoWCY) presents there is low political participation and decision making in Ethiopia. Thus, it highlights the need of inventing new quotas and affirmative actions to change the situation.

To further enhance the impact of affirmative action and quota system for women in politics, there is a need for continued advocacy, awareness campaigns, and capacity-building programs. Strengthening support networks for female politicians, implementing mentorship programs, and addressing structural barriers within political institutions are essential steps towards achieving greater gender parity.

Affirmative action and quota system for women in politics plays a vigorous role in promoting gender equality and empowering women to actively participate in decision-making processes. While progress has been made, ongoing efforts are necessary to address existing challenges and create a more inclusive political landscape that reflects the diversity of Ethiopian society.

Share this post on

Share on facebook
Share on telegram
Share on whatsapp
Share on pinterest
Share on twitter
Share on linkedin
Share on skype
Share on print

Latest Posts