Timran

ትምራን ለመካከለኛ አመራር ሴቶች ለሦስት ቀናት ስትሰጥ የቆየችው ሥልጠና ተጠናቀቀ

ሥልጠናው ‘ሴቶች ለሰላም ግንባታ እና ውትወታ’ በሚል ጭብጥ ከሚያዚያ 30 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ሲካሄድ ቆይቷል።
ግንቦት 02 ቀን 2016 ዓ.ም በተካሄደው የሦስተኛ ቀን ውሎ የሰላም ግንባታ ምንነት፣ አተገባበር፣ ተዋናዮች እንዲኹም ለሰላም ግንባታ የሚኾኑ የውትወታ ስልቶች ጋር የተያያዙ ሐሳቦች ላይ በማተኮር ተሰጥቷል።
በተለያየ መስኮች የተሰማሩ በመካከለኛ አመራርነት ላይ የሚገኙት የሥልጠናው ተሳታፊዎች ሊጠቀሟቸው የሚችሏቸው የውትወታ ነጥቦችም በዝርዝር ቀርበዋል። ማኅበረሰቡን ለሰላም ግንባታ ማነቃቃት፣ በሰላም ግንባታ ሂደት ውስጥ የሴቶችን ተሳትፎ የሚያጠናክሩ የፖሊሲ ማእቀፎች እንዲኖሩ መወትወት፣ በግጭት ወቅት ለሴቶች ጥበቃ እና ከለላ እንዲደረግላቸው መወትወት ተጠቅሰዋል።

በተጨማሪም ሠልጣኞች የውትወታ እቅድ አወጣጥ ሂደቶች ቅደም ተከተል ጋር የተያያዙ ጉዳዮች ላይ ገለጻ ተሰጥቷቸዋል። ከእነዚኽም ውስጥ ተደራሽ አካላትን መለየት፣ ለለየናቸው ተደራሽ አካላት የሚኾን የውትወታ መልእክት ማዘጋጀት፣ ላሰብነው የውትወታ ሥራ የተወሰነ ግብ ማስቀመጥ እና የጊዜ ሰሌዳ ማዘጋጀት ዋና፣ ዋናዎቹ መኾናቸው ተገልጿል።

በመጨረሻም የሥልጠናው ተሳታፊዎች በተሰማሩበት የሥራ መስክ ላይ ከሰላም ግንባታ ጋር በተያያዘ ምን ዓይነት የውትወታ ሥራ መሥራት እንደሚችሉ በመወያየት የድርጊት መርሐ ግብር አዘጋጅተው ለሦስት ቀናት የቆየው ሥልጠና ተጠናቅቋል።

Share this post on

Share on facebook
Share on telegram
Share on whatsapp
Share on pinterest
Share on twitter
Share on linkedin
Share on skype
Share on print

Latest Posts