Timran

ትምራን ለተጨማሪ አንድ ዓመት የጥምረት ለሴቶች ድምፅ በሀገራዊ ምክክር መድረክ ጽ/ቤት ኾና እንድትቀጥል ተወሰነ

ጥምረት ለሴቶች ድምፅ በሀገራዊ ምክክር መድረክ ነሐሴ 26 ቀን 2015 ዓ.ም ባካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ ትምራን ለቀጣይ ተጨማሪ አንድ ዓመት ጽ/ቤት ኾና እንድትቀጥል በሙሉ ድምፅ ወሰነ።

በጠቅላላ ጉባኤው የተገኙ 35 አባል ድርጅቶች የጥምረቱ ሰባት ሥራ አስፈጻሚ ድርጅቶች ሓላፊነታቸውን ለአንድ ዓመት እንዲቀጥሉ፣ የኢትዮጵያ ሴቶች መብቶች ተሟጋች እና መቀመጫውን ሶማሌ ክልል ያደረገው ኡጋሶ የተሰኙ ኹለት ድርጅቶች ደግሞ ተጨማሪ ሥራ አስፈጻሚ እንዲኾኑ ወስኗል።

ከዚኽ በተጨማሪ ሰባት አዳዲስ አባል ድርጅቶችን ለመቀበል ባደረገው ውይይት ሐረሪ መድኅን ኤችአይቪ ፖዘቲቭ ሴቶች ማኅበር (ሐረር)፣ የእናቶች እና ሕፃናት መብቶች ድርጅት (MCRO/ሶማሌ)፣ ኮንሰርን ፎር ኢንተግሬትድ ዴቨሎፕመንት (አዲስ አበባ) እንዲኹም እናቶች ለእናቶች (Mums for Mums/ትግራይ) የተሰኙ አራት ድርጅቶችን በአባልነት ተቀብሏል፤ ቀሪዎቹ ድርጅቶች ላይ በሥራ አስፈጻሚ በኩል ማጣራት ተደርጎ ውሳኔ ይሰጣቸው ተብሏል።
በዕለቱ የጥምረቱ የአንድ ዓመት አጠቃላይ የሥራ አፈጻጸም እና የቀጣይ ዓመት እቅድ ከበጀት ጋር ቀርቦ ሰፊ ውይይት ከተደረገ በኋላ ግብአት ታክሎበት ጸድቋል።

Share this post on

Share on facebook
Share on telegram
Share on whatsapp
Share on pinterest
Share on twitter
Share on linkedin
Share on skype
Share on print

Latest Posts