ጥምረት ለሴቶች ድምፅ በሀገራዊ ምክክር መድረክ መጋቢት 2014 ዓ.ም ሴቶች በሀገራዊ ምክክር ሂደት ውስጥ ተገቢ ውክልና እንዲኖራቸው ለማስቻል የተቋቋመ ሲኾን፣ በአኹኑ ወቅት ከ50 በላይ አባል ድርጅቶችን ይዞ ይንቀሳቀሳል።
እኛ ጥምረት ለሴቶች ድምፅ በሀገራዊ ምክክር መድረክ አባል ድርጅቶች ለመላው ኢትዮጵያውያን እንኳን ለ2016 ዓ.ም የዘመን መለወጫ በዓል በሰላም አደረሳችኹ እያልን አዲሱ ዓመት ሀገራችን ኢትዮጵያ ሰላሟ የሚትረፈረፍበት ዓመት እንዲኾን መልካም ምኞታችንን አስቀድመን እንገልጻለን።
በሀገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ ከተለያዩ አቅጣጫዎች የሚሰሙት የትጥቅም ሆነ ያለ ትጥቅ የሚደረጉ ግጭቶች ሴቶች ላይ የሚያሳድሩት ተፅዕኖ እጅግ ከባድ እና በቀላሉ ሊሽር የማይችል ጠባሳን ጥለው የሚሄዱ መኾኑ እሙን ነው። ይኽም ሊኾን የቻለው በሀገሪቱ ውስጥ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተስተዋለ የመጣው የሴቶችን ሰውነት የጦር መሣሪያ አድርጎ የመጠቀም ተግባር እየተባባሰ በመምጣቱ የተነሣ ነው። ይኽ ደግሞ የሴቶች ስቃይ እና የፍትሕ እጦት አዙሪት እንዲቀጥል እንዲሁም መሠረታዊ የሰብአዊ መብቶች እንዲጣሱ ያደርጋል።
በመኾኑም እኛ የጥምረቱ አባል ድርጅቶች በአዲሱ ዓመት እዚህም እዚያም ያሉ ግጭቶች እንዲቆሙ እና መንግሥት ለችግሮቻችን ሰላማዊ የግጭት መፍቻ መንገዶችን እንዲፈልግ ብሎም እንዲጠቀም ስንል የሰላም ጥሪ እናስተላልፋለን።
የሰላም ጥሪውን ያቀረቡ የጥምረት ለሴቶች ድምፅ በሀገራዊ ምክክር አባል ድርጅቶች
• ሐረሪ መድኅን ኤችአይቪ ፖዘቲቭ ሴቶች ማኅበር-ሐረሪ ክልል
• ሙጀጀጓ ሎካ የሴቶች ልማት ማኅበር-ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል
• ሮሺ ወዱ ፓስቶራል ውሜን ዴቨሎፕመንት አሶሴሽን-አፋር ክልል
• ሲቄ የሴቶች ልማት ማኅበር
• ሲነርጂ ፎር ኮሙዩኒቲ ዴቨሎፕመንት-ድሬዳዋ
• ሳራ ፍትሕ ከሁሉም ሴቶች ማኅበር
• ሴታዊት ንቅናቄ
• ስብስብ ለሰብአዊ መብቶች በኢትዮጵያ
• ሶማሌ ውሜን ዲያሎግ ስፔስ-ሶማሌ ክልል
• ሶማሌ ነን ስቴት አክተርስ ኮአሊሽን-ሶማሌ ክልል
• ራስ አገዝ የሴቶች ድርጅት
• ቁማን ውሜን ዴቨሎፕመንት አሶሴሽን-ሶማሌ ክልል
• ተርካንፊ ለዘላቂ ልማት-ኦሮሚያ ክልል
• ትምራን
• ኒው ሚሌኒየም ውሜን ኢምፓወርመንት ኦርጋናይዜሽን
• አሶሴሽን ፎር ውሜንስ ሳንክቹዋሪ ኤንድ ዴቨሎፕመንት
• አድቮኬሲ ሴንተር ፎር ዴሞክራሲ ኤንድ ዴቨሎፕመንት
• ኢምፓቲ ፎር ላይፍ ኢንተግሬትድ ዴቨሎፕመንት አሶሴሽን
• ኢስት አፍሪካ ኢንሺየቲቭ ፎር ቼንጅ (I4C)
• ኢንተር አፍሪካ ግሩፕ
• እናቶች ለእናቶች/Mums for Mums-ትግራይ ክልል
• ኮንሰርን ፎር ኢንተግሬትድ ዴቨሎፕመንት
• ወጣት ሴቶች ሀገር አቀፍ የበጎ አድራጎት ድርጅት
• ውሜን ካን ዱ ኢት
• የሐረሪ ክልል ሴት አካል ጉዳተኞች ማኅበር
• የሕግ ባለሞያዎች ለሰብአዊ መብቶች
• የመብቶች እና ዴሞክራሲ እድገት ማእከል
• የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሴቶች ማኅበር
• የአማራ ክልል ሴቶች ማኅበር
• የአዲስ አበባ ሴቶች ማኅበር
• የአፋር ክልል ሴቶች ፌዴሬሽን
• የኢትዮጵያ የሕግ ባለሞያ ሴቶች ማኅበር (ኢ.ሕ.ባ.ሴ.ማ)
• የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ተሟጋቾች ማእከል
• የኢትዮጵያ ሴቶች ማኅበራት ቅንጅት
• የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኛ ሴቶች ብሔራዊ ማኅበር
• የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኀን ሴቶች ባለሞያዎች ማኅበር (ኢት.መ.ሴ.ባ.ማ)
• የኢትዮጵያ ሴቶች መብት ተሟጋች (ኢሰመተ)
• የኢትዮጵያ ሠራተኛ መብቶች ተሟጋች
• የኦሮሚያ ክልል ሴቶች ማኅበር
• የእናቶች እና ሕፃናት መብቶች ድርጅት-ሶማሌ
• የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ሴቶች ማኅበር
• የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሴቶች ማኅበር
• የድሬዳዋ መምህራን ማኅበር
• የድሬዳዋ ሴቶች ፌዴሬሽን
• የጋምቤላ ክልል ሴቶች ማኅበር
• ጋድ ፎር ፒፕል ሪሊፍ ኤንድ ዴቨሎፕመንት ኦርጋናይዜሽን
• ጣሊታ ራይዝ አፕ-ሲዳማ ክልል
• ፋሚሊ ሰርቪስ አሶሴሽን
• ፎረም ፎር አፍሪካን ውሜን ኢጁኬሽናሊስትስ
• ፒስ ኤንድ ዴቨሎፕመንት ኢትዮጵያ
ጳጉሜን 05 ቀን 2015 ዓ.ም