Timran

የሽግግር ፍትሕ ምንነት

የሽግግር ፍትሕ ማኅበረሰቦች ለመጠነ ሰፊ እና ስር የሰደዱ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች የሚሰጡትን ምላሽ የሚመለከት ጉዳይ ነው። በዚኽም እጅግ አስቸጋሪ የሚባሉ የሕግ፣ የፖለቲካ እና ማኅበራዊ ሳይንስ ጥያቄዎችን ያነሣል ብሎም ስፍር ቁጥር የሌላቸው ግራ አጋቢ ጉዳዮችን ለመፍታት ይጥራል። በጥቅሉ የሽግግር ፍትሕ ለተጠቂዎች ይቆማል።

ሰዎች ወላጆቻችን፣ ወንድሞቻችን፣ እኅቶቻችን አልያም ልጆቻችን ሊኾኑ ይችላሉ በጭካኔ ሊገደሉ ወይም ሊጠፉ፣ በቃላት ሊገለጽ የማይችል የመብት ጥሰት ሊፈጸምባቸው ወይም ሊገረፉ፣ ጾታዊ ጥቃት ሊፈጸምባቸው ወይም የትውልድ ቀዬአቸውን ወይም ሀብት ንብረታቸውን ለቅቀው ለመሰደድ ሊገደዱ እና የሽብር ተግባር ሊፈጸምባቸው ይችላል። በአንድ አካባቢ የሚገኝ ማኅበረሰብ በማንነቱ፣ በዘሩ፣ በእምነቱ፣ በያዘው የጾታ ምንነት ወይም የፖለቲካ አቋም የተነሣ ሙሉ በሙሉ ሊጠፋ ወይም ሊገደል ይችላል። በሌላ በኩል ማኅበረሰቡ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ መብቶችን ጨምሮ ኹሉንም ዓይነት መብቶቹን ሊነጠቅ እና ከኅብረተሰቡ ተገልል እንዲኖር ሊደረግ ይችላል።

እያንዳንዱ ኹኔታ የተለየ በመኾኑ በዓለም ላይ የሚገኙ ኅብረተሰቦች እና ግለሰብ ባለድርሻ አካላት ወደ ሰላም፣ እውነት እና ኹሉን አቀፍ ነገ መንገድ ለመሸጋገር ጉዳዩ ኾኗል አልኾነም፣ መቼ እና እንዴት ተፈጸሙ ለሚሉ ለእያንዳንዱ ተመሳሳይ እና አስቸጋሪ ጥያቄዎች ለተፈጸሙት ወንጀሎች እውቅና መስጠት እና ማስተካከል ብሎም ዜጎች እና መሪዎች ብጥብጥ እና የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ዳጋም እንደማይፈጸሙ ስምምነት ላይ መድረስ አለባቸው።

ጉዞው ረጅም እና አስቸጋሪ የተጠቂዎችንና ከኹሉም የኅብረተሰብ ክፍል የተውጣጡ አካላትን ትርጉም ያለው ተሳትፎ የሚጠይቅ ነው።

ከኹሉም በላይ የሽግግር ፍትሕ ለተጠቂዎች ትኩረት ይሰጣል። እንደ ዜጋ እና ሰብአዊ ፍጡር መብታቸው እና ክብራቸውን መጠበቅ ላይ ያተኩራል፤ ለተፈጸመባቸው ጉዳት ተጠያቂነት፣ እውቅና መስጠት እና የማስተካከያ እርምጃ መውሰድ ላይ ይሠራል። ተጠቂዎችን ማእከል በማድረግ እና ለክብራቸው ቅድሚያ በመስጠት፣ የሽግግር ፍትሕ ኹሉም ዜጎች የተካተቱበት እና የእያንዳንዱ መብት የተጠበቀበት የታደሰ ማኅበራዊ ውል እንዲኖር ይጥራል።

የሽግግር ፍትሕ ሰዎች በጋራ ተሰባስበው ቀደም ሲል ለተፈጸሙ አሰቃቂ ወንጀሎች ወይም በተደጋጋሚ የሚከሰቱ አጥፊ ግጭቶች እንዲቆሙ በርካታ አማራጮችን በማቅረብ መፍትሔ ለመስጠት የሚጥሩበት ስልት ነው። መፍትሔዎቹም ኅብረተሰቡ የሚገዛባቸው የፍትሕ እና የፖለቲካ ሥርዓቶች እና ተቋማት ላይማሻሻያ ማድረግ እንዲሁም ምን ተፈጠረ፣ ለምን ተፈጠረ የሚለውን እውነታ ለማውጣት እና የታሰሩ አልያም በግዳጅ እንዲሠወሩ የተደረጉ ሰዎች ዕጣ ፈንታ መወሰን ያካተቱ ሊኾኑ ይችላሉ። በተጨማሪም አጥፊዎች እንዲጠየቁ ለማስቻል ብሔራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ክሶችን ጨምሮ የፍርድ እና ፍርድ ነክ ያልኾኑ ሂደቶችን ሊያካትቱ ይችላሉ። ለተጎጂዎች የገንዘብ ማካካሻ፣ ጡረታ፣ ንብረት መተካት ወይም የሲቪል እና ፖለቲካ መብቶቻቸውን መመለስ፣ የጤና እና ትምህርት እድል መስጠት፣ ለተጎጂዎች ጉዳቶች እና መብት ጥሰቶቻቸው እውቅና መስጠት እና መገንዘብ የመሳሰሉ የካሣ ክፍያዎችን ሊይዝ ይችላል።

እነዚኽ ምላሾች በተናጠልም ይኹን በጥምረት ከተፈጸሙ ኅብረተሰቡ ከግጭት ወደ ዘላቂ ሰላም፣ ከአምባገነን አገዛዝ ወደ ዴሞክራሲ፣ ከብዙኀን መብቶች ጥሰቶች ወደ ሰብአዊ መብቶች መከበር፣ ከተጠያቂነት ባሕል አለመኖር ወደ የዜጎች ክብር መጠበቅ ሽግግር እንዲኖር እገዛ ያደርጋሉ። የሽግግር ፍትሕ ይዘቶች አኹንም በጦርነት ውስጥ በሚገኙ፣ በቅርቡ ከግጭት እና ጭቆና በወጡ እና የዳበረ ዴሞክራሲ ኖሯቸው ስልታዊ ዘረኝነት እና መገለል ጋር የተያያዘ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ባሉባቸው ሀገራት ይተገበራሉ። ነገር ግን የሽግግር ፍትሕ ሂደቶች አተገባበር በቀላሉ የሚፈጸሙ አይደለም፤ ዓመታትን ሊወስዱ ይችላሉ። የተለመደው ችግር ቅደም ተከተሎቹን ማዋቀር ወይም መደርደር ነው። ሌላኛው ችግር ሂደቶቹ በተጀመሩበት እንቅስቃሴ፣ አቅም እና ቀናነት ደረጃ መዝለቅ አለመቻል ነው።

በጥቅሉ የሽግግር ፍትሕ አንድ ጉዳይ፣ አንድ ሂደት አልያም አንዱ መፍትሔ ለኹሉም ተቋማት ተገልብጦ የሚሠራበት አይደለም። ይልቁንም የሽግግር ፍትሕ እንደ ካርታ ወይም የመንገዶች ትስስር ወደምነፍለገው መዳረሻ የሚወስደን፣ እጅግ ሰላማዊ፣ እውነተኛ እና ኅብረተሰብ አካታች ያለፉ ጥፋቶችን የሚያርም እና ለተጠቂዎች ፍትሕ የሚሰጥ ሂደት ነው። የሽግግር ፍትሕ ብቸኛ መንገድ የለውም። ይልቁንም እንደተፈጸሙ በደሎች ብሎም እንደ ኅብረተሰቡ ባሕል፣ ታሪክ፣ ሕጋዊ እና ፖለቲካ መዋቅር፣ ችግር የመፍታት አቅም እንዲሁም ዘውግ፣ ሃይማኖት እና ማኅበረኢኮኖሚያዊ ስብጥር ሁኔታየተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች የተለያዩ አካሄዶችን የሚጠቀሙበት ስልት ነው። በመኾኑም የሽግግር ፍትሕ ኅብረተሰቡ በዚኽ መንገድ ላይ ምን ያህል ርቀት እና በምን ያህል ፍጥነት ተጉዞ ከመንግሥት አካላት እና ፖለቲከኞች እስከ ተጎጂዎች፣ መያዶች እና መደበኛ ዜጎች የተካተቱበት ባለድርሻ አካላት ችግሮችን መፍታት፣ እልህ አስጨራሽ ጥረት ማድረግ እና መተባበር ይችላሉ ለሚለው ምላሽ የሚሰጥ ሂደት ነው።

What Is Transitional Justice?

Transitional justice refers to how societies respond to the legacies of massive and serious human rights violations. It asks some of the most difficult questions in law, politics, and the social sciences and grapples with innumerable dilemmas. Above all, transitional justice is about victims.

People just like our parents, our brothers, and sisters, our children brutally murdered or disappeared, subjected to untold abuses or torture, sexual or gender-based violence, or forced to flee their homes and everything they built and ever knew in terror. The whole communities were massacred or persecuted because of their ethnicity, race, faith, gender or sexual orientation, or political affiliation. Communities have been systematically deprived of all their rights, including social and economic ones, and forced to live on society’s margins.

While every context is unique, societies and individual stakeholders the world over must find answers to the same difficult questions about whether, when, and how to embark on a path toward a peaceful, just, and inclusive future where past crimes have been acknowledged and redressed and citizens and leaders agree that violence and human rights abuses can never again happen. The journey is a long and challenging one that requires the meaningful participation of victims together with all sectors of society.

Above all, transitional justice is about victims. It focuses on their rights and dignity as citizens and human beings and it seeks accountability, acknowledgment, and redress for the harm they suffered. By putting victims at the center and their dignity first, transitional justice signals the way forward for a renewed social contract in which all citizens are included and everyone’s rights are protected.

Transitional justice involves people coming together to address the legacies of horrendous atrocities, or to end recurring cycles of violent conflict, by developing a range of responses. These responses may include reforms of the legal and political systems and institutions that govern a society, as well as mechanisms for uncovering the truth about what happened and why and for determining the fate of those who were detained or forcibly disappeared. They may include judicial and non-judicial processes, such as national or international criminal prosecutions to hold perpetrators accountable. They may also include initiatives for providing reparations to victims, which can take multiple forms such as financial compensation, pensions, restitution of property or civil and political rights, access to health care or education, and acknowledging and memorializing the victims and the abuses they suffered.

These responses, whether implemented alone or in combination, help a society transition from conflict to sustainable peace, from authoritarianism to democracy, from a legacy of mass human rights abuses to respect for human rights, and from a culture of impunity to one in which citizens are treated with dignity. They are applicable in countries still torn apart by war, in those emerging from conflict or repression, and in developed democracies dealing with unaddressed human rights violations associated with systemic racism and marginalization. These processes are not easy to implement, however, and can take years. One common challenge is how to structure or sequence the steps. Another is maintaining the initial momentum, energy, and optimism while pushing for processes that may take a long time to complete.

Transitional justice is not one thing or one process, nor is it a one-size-fits-all formula to replicate institutions. Instead, transitional justice is more like a map and network of roads that can bring you closer to where you want to go: a more peaceful, just, and inclusive society that has come to terms with its violent past and delivered justice to victims. There is no one route. Instead, different societies take different routes, depending on the nature of the atrocities that occurred and the particularities of that society, including its culture, history, legal and political structures, and capacity, as well as its ethnic, religious, and socioeconomic makeup. How far along and how quickly a society travels along this path depends on the resolve, tireless effort, and collaboration of many stakeholders from government actors and politicians to victims, civil society organizations, and ordinary citizens. (Source: www.ictj.org)

Share this post on

Share on facebook
Share on telegram
Share on whatsapp
Share on pinterest
Share on twitter
Share on linkedin
Share on skype
Share on print

Latest Posts

Archives


Categories