የትምራን ጊዜያዊ ሥራ አስፈጻሚ ማኅደር ዳዲ ጥቅምት 08 ቀን 2016 ዓ.ም በኢትዮጵያ የፌዴራላዊ ጀርመን መንግሥት ኤምባሲ ተገኝተው ከፖለቲካ ጉዳዮች አንደኛ ጸሐፊ ከኾኑት ቫኔሳ ፕሪንዝ ጋር ውይይት አካሄዱ።
ሥራ አስፈጻሚዋ ትምራን የተመሠረተችበትን ራእይ እና እያከናወነቻቸው የሚገኙ ተግባራትን በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በተጨማሪም ትምራን ከጀርመን ኤምባሲ ጋር በጋራ ለመሥራት ፍላጎት እንዳላት ገልጸዋል።
የኤምባሲው የፖለቲካ ጉዳዮች ጸሐፊዋ በበኩላቸው ቀደም ባሉት ጊዜያት ስለ ትምራን ተግባራት መረጃ እንዳላቸው ገልጸው፣ ወደፊት የምታከናውናቸውን ተግባራት ለመደገፍ የሚቻልባቸው መንገዶች ካሉ ለበላይ ሓላፊዎች እንደሚያቀርቡ ተናግረዋል።
TIMRAN Interim Executive Directress discussed with the Political Affairs First Secretary at the Embassy of the Federal Republic of Germany
TIMRAN Interim Executive Directress (ED) Mahder Dadi discussed with the Political Affairs First Secretary Vanessa Prinz at the Embassy of the Federal Republic of Germany in Ethiopia on October 19, 2023.
The ED briefed about TIMRAN’s vision and the activities she is doing these days. In addition, she expressed TIMRAN’s interest in working with the German Embassy.
The Political Affairs First Secretary on her part said she had information about TIMRAN activities, and in the future, if there is any means to support TIMRAN activities she will table her request to the Embassy leadership.