Timran

ጥምረት ለሴቶች ድምፅ በሀገራዊ ምክክር መድረክ በሐረሪ ክልል ያዘጋጀው የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ተጠናቀቀ


ጥምረት ለሴቶች ድምፅ በሀገራዊ ምክክር መድረክ በሐረሪ ክልል የሚገኙ ሴቶች በሀገራዊ ምክክሩ ላይ ትርጉም ባለው መልኩ እንዲሳተፉ ለማስቻል ለአራት ቀናት ያዘጋጀው የግንዛቤ ማስጨበጫ ምክክር መድረክ ግንቦት 25 ቀን 2015 ዓ.ም ተጠናቀቀ።

በአራተኛ ቀን መርሐ ግብር ላይ ከክልሉ ዘጠኝ ወረዳዎች እና የተለያዩ ቢሮዎች የተውጣጡ ከ50 በላይ ሴቶች ተሳታፊ ሆነዋል።

የጥምረት ለሴቶች ድምፅ በሀገራዊ ምክክር መድረክ የፕሮግራም አስተባባሪ አቶ አስቻለው ማቴዎስ ለተሳታፊዎች የእንኳን ደኅና መጣችኹ በማለት የግንዛቤ ማስጨበጫ እና ምክክር መድረኩን በንግግር ከፍተዋል።

በንግግራቸውም ጥምረት ለሴቶች ድምፅ በሀገራዊ ምክክር መድረክ በዋናነት ሴቶች ጉዳይ ላይ በሚሠተሩ 22 አባል ድርጅቶች ከአንድ ዓመት በፊት ተመሥርቶ፣ በአሁኑ ወቅት ሐረሪ ክልል የሚገኙ አባላት ጨምሮ ከ50 በላይ ድርጅቶች ያቀፈ መሆኑን ገልጸዋል።

በቅርቡም በሶማሌ ክልል በነበረ የልምድ ልውውጥ መድረክ ላይ ተጨማሪ ሁለት አባል ድርጅቶች ከጥምረቱ ጋር ለመሥራት መጠየቃቸውንና በተመሳሳይ መልኩ ከሐረሪ ክልል አዳዲስ አባል ድርጅቶች የጥምረቱ አባል ለመሆን ሂደት ላይ እንደሚገኙ ጠቅሰዋል።

አያይዘውም ጥምረት ለሴቶች ድምፅ በሰባት የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የሚመራ መሆኑንና ትምራን በጽ/ቤትነት እያገለገለች መሆኗን አንሥተዋል።

ጥምረቱ ሴቶች በሀገራዊ ምክክር ላይ ንቁ ተሳታፊ እንዲሆኑ እና ድምፃቸው በአግባቡ እንዲሰማ ለማድረግ ከመላው ሀገሪቱ ከሚገኙ አባል ድርጅቶች ለተውጣጡ 150 ሴቶች የአመቻችነት ሥልጠና መስጠቱን ተናግረዋል።

እነዚኽን አመቻቾች በመጠቀም በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል እና አሶሳ ዞኖች ውስጥ ለሚገኙ ወረዳ ነዋሪ ሴቶች የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሐ ግብሮች ማዘጋጀቱን ተናግረዋል።

የሐረሪ ክልል የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ እንዲሁ ባለፉት ሦስት ቀናት ሲከናወን ቆይቶ በአራተኛ ቀን ላይ የማጠቃለያ መርሐ ግብር የሚከናወን መሆኑንና ጠቅሰው፣ እንደ ክልል ለሀገራዊ ምክክር የሚጠቅሙ ሐሳቦችን እንዲያንሸራሽሩ ጠይቀዋል።

የመድረኩ ተሳታፊዎች ስለ ሀገራዊ ምክክር ምንነት የመግቢያ ገለጻ ተሰጥቷቸው የቡድን ውይይት በማድረግ ሐሳባቸውን አንጸባቀዋል፤ ለተሰጣቸው እድል ምስጋና አቅርበዋል፤ በማጠቃለያ ላይ እናቶች ምርቃት ሰጥተው መርሐ ግብሩ ተደምድሟል።

Share this post on

Share on facebook
Share on telegram
Share on whatsapp
Share on pinterest
Share on twitter
Share on linkedin
Share on skype
Share on print

Latest Posts